የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሁን የሚገኝበት ምድረ ግቢ የተለያዩ የሕብረተሰብና የእንስሳ ጤና አገልግሎት መስጠት የጀመረው እ.አ.አ.በ1922 ( እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1914) ዶ/ር ቶማስ ላምቤ (Dr.Thomas Lambie) የተባሉ አሜሪካዊ የበጎ ፈቃድ ህክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ከአቋቋሙበት ጊዜ ጅምሮ ነው፡፡ ዶ/ር ቶማስ ላምቤ አገልግሎቱን ሲጀምሩ አብረዋቸው በመጡት አራት ሀኪሞችና ስድስት ነርሶች ነበር አገልግሎት መስጠት የጀመሩት፡፡ በጊዜው ዶ/ር ቶማስ ላምቤ የጤና አገልግሎት ብቻም ሳይሆን በአገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ሴቶች ብቻ የሚማሩበት የአሜሪካን ሚሽን ተብሎ ይጠራ የነበረውን ትምህርት ቤትም በመክፈት ሴቶችን ማስተማር ጀምረው ነበር፡፡ ይህ አገልገሎታቸው እስከ ጣሊያን ወረራ ማለትም  እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1928 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ የቆዬ ሲሆን የምድረ ግቢውና የአካባቢው መጠሪያም ዶ/ር ላምቤ ሆስፒታል በሚል ይጠራ ነበር፡፡
የጣሊያን መንግስት አገራችንን በወረራ በያዘበት ጊዜ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩትን የውጪ አገር ዜጎች ይዞታና ንብረት ካሳ በመስጠት ከአገር እንዲወጡ በመደረጉ ዶ/ር ቶማስና ባልደረቦቻቸውም ወደ አገራቸው አሜሪካ ሄዱ፡፡ በምድረ ግቢው ይሰጡ የነበሩት አገለግሎቶችም ተቋረጡ፡፡በምትኩ ግቢውን የጣሊያን አስተዳደር ለአዲስ አበባ ሳኒተሪያን መቆጣጠሪያ አገለግሎት ሲጠቀምበት ቆየ፡፡
የጣሊያን መንግስት በላምቤ ሆስፒታል ይሰጥ የነበረውን አገለግሎት በወቅቱ በሆስፒታሉ ይሰሩ የነበሩትን ኢትዮጵያውያን እና የራሱን ባለሙያዎች በመጨመር የኢትዮጵያ ኢምፔሪያል ጥናት ኢንስቲትዩት በማለት አሁን የጦር ሀይሎች ሆስፒታል ወደ ሚገኝበት ቦታ ተዛወሮ የተወሰነ አገለግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ሞክሮ ነበር፡፡ ቀጥሎም አሁን አውራ ጎዳና ባለስልጣን መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት አካባቢም እንዲዛወርም አደርጎት ነበር፡፡
ጣሊያን ተሸንፎ ከአገራችን ሲወጣ ከጣሊያን ወረራ በፊት በውጪ አገር ባለሙያዎች የተለያዩ አገለግሎቶች ሲሰጡ የነበሩ ተቋማት ወደ ቤተመንግስት ንብረትነት እንዲዛወሩ ተደረገ፡፡ በዚህም ምክንያት የቀድመው ላምቤ ሆስፒታል ተፈሪ መኮንን ሆ/ል የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ለንጉሳዊያን ቤተሰብ መታከሚያነት እንዲያገለግል ተደርጎ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ 1943 ዓ.ም ድረስ ይህንኑ አገልግሎት ሲሰጥ ቆዬ፡፡ በ1943 የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በአዋጅ ሲቋቋም በምድረ ግቢው ይሰጥ የነበረው የህክምና አገለግሎት ቀርቶ በጤና ሚኒስቴር ስር እንዲተዳደር በማድረግ የጤና ሚኒስቴርም ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በተለያዩ በሽታዎች ላይ ምርምርና ጥናት ለማካሄድ እንዲሁም የጤና ላቦራቶሪ ምርመራ አገለግሎት ለመስጠት በተደረገ ስምምነት በ1944 ዓ.ም “ኢንስቲትዩት ፓስተር ደ’ኢትዮጲ” በሚል መጠሪያ ተሰይሞ የተለያዩ መምሪያዎችን በማቋቋም ስራውን ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ስራውን የሚመሩት ከሁለቱም መንግስታት የተውጣጡ ባለሙያዎች ነበሩ፡፡ ጥናትና ምርምር እንዲካሄድባቸው የተቋቋሙት መምሪያዎችም፡

  1. የባክቴሮሎጂ፣ ፓራሳይቶሎጂ እና ሴሮሎጂ መምሪያ፣
  2. የኬሚካል አናሊሲስ መምሪያ፣
  3. የአንቲፓትሪዮቲክ ክትባት ማዘጋጃ መምሪያ፣
  4. የታይፈስ ክትባት ማዘጋጃ መምሪ፣
  5. የቲቢ በሽታ ክትባት ማዘጋጃ መምሪያ፣
  6. የእብድ ውሻ በሽታ ክትባት ማዘጋጃ መምሪያ እና
  7. የማይክሮቪያል ክትባት ማዘጋጃ መምሪያ የሚባሉ ነበሩ፡፡

በወቅቱ በተለያዬ መጠን ይመረቱ ከነበሩት ክትባቶችም፡

  1. አንቲ-ቪሪዮሊክ ክትባት
  2. አንቲ-ታይፈስ፣
  3. የእብድ ውሻ መከላከያ ክትባት፣
  4. የቲቢ በሽታ ክትባት፣
  5. የታይፎይድ ክትባት፣
  6. የቢጫ ወባ ክትባት
  7. የጉንፋን በሽታ ክትባት ይገኙበታል፡፡ በየአመቱም የተወሰነ መጠን እየተመረተ አገልግሎቱ በነጻ ለሕብረተሰቡ ይሰጥ ነበር፡፡

ይህ በፈረንሳይና በኢትዮጵያ መንግስት ስምምነት የተጀመረው የምርምርና ጥናት እንዲሁም የተለያዩ ክትባቶች በማምረት በነጻ የመስጠቱ ተግባር እስከ 1957 ዓ.ም ድረስ ዘልቋል፡፡አሁን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኝበት ጊቢ ከ1915 እስከ 1928 ዓ.ም ድረስ ዶ/ር ቶማስ ላምቤ ሆስፒታል በሚል ሲጠራበት ቆይቶ የነበረው ስያሜ ከ1944 እስከ 1957 በዘለቀው አገለግሎት ማለትም ኢንስቲትዩት ፓስተር ደ’ኢትዮጲ በሚል ስያሜ ደግሞ ምንም እንኳ ከዚያ ወዲህ የተለያዩ ስያሜዎች ቢሰጡትም እስካሁን ድረስ ፓስተር ኢንስቲትዩት የሚለው በብዙ ህዝብ ዘንድ እየተጠራበት ይገኛል፡፡

ከ1957 ዓ.ም በኋላ በኢትዮጵያ መንግስትና በፈረንሳይ መንግስት መካከል የነበረው ስምምነት ሲቆም ሙሉ በሙሉ አስተዳደሩም ሆነ ሰራተኛው ኢትዮጵያውያን ብቻ እንዲመሩትና በጀቱም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት መሸፈን ሲጀምር መጠሪያ ስሙም የኢትዮጵያ የዋናው ላቦራቶሪና የጥናት ድርጅት ተባለ፡፡ ቀደም ሲል ይሰጥ የነበረው አገለግሎትም ቀጥሎ እስከ 1977 ዓ.ም ድረስ በዚሁ ስያሜ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት በስተቀር ሌሎች የክትባት አገለግሎቶች ከደርግ መንግስት መምጣት በኋላ  አልቀጠሉም፡፡

 ከ1957 ዓ.ም በኋላ በተለይ ተላላፊ በሆኑና ድንገት በሚከሰቱ የህብረተሰቡ የጤና ችግሮች ላይ ይደረግ የነበረው ምርምርና ጥናት ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር፡፡ ለአብነትም በ1973 ዓ.ም በቀድሞው ወሎ ክፍለ ሀገር ተከስቶ የነበረውን የኤርጎይቲዝም በሽታ መንስኤ ለማወቅ የተቻለው በዚሁ ኢንስቲትዩት በተደረገ ጥናትና ምርምር ነበር፡፡

ከ1977 ዓ.ም ወዲህ የኢንስቲትዩቱ ሥራ እያደገ በመምጣቱ በአዲስ መልክ ኢንስቲትዩቱን እንደገና መዋቀር በማስፈለጉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት በሚል በአዋጅ እንደገና ተቋቋመ፡፡ ኢንስቲትዩቱን ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በዳይሬክተርነት የመሩት ዶ/ር ፍስኃ ኃይለመስቀል ለኢንስቲትዩቱ ሁለንተናዊ እድገትና ከዓለም ዓቀፍ መሰል ተቋማት ጋር ያለው ግንኙነት እንዲሻሻልና እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡  ኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ቴከተኖሎጂ ትምህርት ቤትንም በዚህ ጊዜ ከፍቶ በርካታ የዘርፉ ሙያተኞችን አፍርቷል፡፡

በመጀመሪያ የሕጻናት ሥነ- ምግብ ክፍል ተብሎ በኢትዮጵያ መንግስትና በስዊድን መንግስት ትብብር በ1962 ዓ.ም ነበር የተቋቋመው፡፡ ይህ የሥነ-ምግብ ክፍል በ1968 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ ኢንስቲትዩት ተብሎ ተቋቋመ፡፡ ቢሮውም በቀድሞው ልእልት ተናኜወርቅ ሆስፒታል በአሁኑ የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ነበር፡፡  ከ1968 ዓ.ም እስከ 1973 ዓ.ም ይህ ኢንስቲትዩት በአገራችን ተከስቶ የነበረውን ድርቅ ለመቋቋም በተደረገው እንቅስቃሴ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡በወቅቱ የእርዳታ ማቋቋሚያና ማስተባባሪያ ጽ/ቤት እንዲቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የዶቤና እድገት በሚል ስያሜ የተጨማሪ ምግቦች ቁጥር እንዲያድግ አድርጓል፡፡ከ1973 ዓ.ም ወዲህ በዋናው ላቦራቶሪና የጥናት ድርጅት በሚገኘው ግቢ ውስጥ የራሱን ሕንጻ ገንብቶ በአብዛኛው በምግብ ሣይንስና ኒውትሪሽን ምርምር ላይ በማተኮር በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ ኢንስቲትዩቱን ለረዢም ጊዜ በዳይሬክተርነት የመሩት ዶ/ር ዘውዴ ወልደ ገብርኤል ለኢንስቲትዩቱ እድገት በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

የባህል መድሀኒት መምሪያ በ1979 ዓ.ም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡ የመምሪያውን አሰራር የበለጠ ለማጠናከር የባህል መድሀኒት መምሪያ ተብሎ የተቋመውን መምሪያ ወደ የባህል መድሀኒት ምርምር መምሪያነት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ መምሪያው ከተቋቋመ ጀምሮ በተለይ በአገራችን የሚገኙ የባላዊ መድሀኒቶችን አገራዊ መጠሪያና ሣይንሳይ ስያሜ በማጥናትና በማጠናቀር ከ600 በላይ ዕጽዋቶችን በዘመናዊ መንገድ እንዲታተም አድርጓል፡፡ በተለያዩ የባህል መድሀኒቶችም ላይ በርካታ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡( ዶ/ር ይልማ ደስታ ለባህል መድሀኒት ምርምር እድገት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል)፡፡

ከኢህዲግ መንግስት መመስረት በኋላ በጤናው ዘርፍ ተመሳሳይና ተቀራራቢ ተግባራት ማለትም ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት በአንድ ላይ ቢዋቀሩና ተጋግዘው እንዲሰሩ ቢደረግ ከሀብት አጠቃቀምና የእውቀት ሽግግርን ከማጠናከር አንጻር የሚኖረው ፋይዳ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ሶስቱን ተቋማት በአንድ ላይ በማድረግ በ1987 ዓ.ም እንደገና የኢትዮጵያ የጤናና ሥነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት በሚል ተቋቋመ፡፡ ድርጅቶችም 1/ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ 2/ የኢትዮጵያ ምግብ ጥናት ድርጅት እና 3./የባህል መድሀኒት ምርምር መምሪያ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ የጤና እና ሥነ-ምግብ ኢንስቲትዩት በአዲስ መልክ ሲቋቋም የተሰጠው ተልእኮ በዋነኛነት የቅድሚያ ትክረት በተሰጣቸው የሕብረተሰብ ጤና ችግሮች ላይ ችገር ፈቺ ምርምሮችን በማካድድ ተአማኒነት ያለው የጤና መረጃ ለውጤታማ ውሳኔዎች ለፖሊሲ ውሳኔ ሰጪ አካላት ማቅረብ ነበር፡፡ በተጨማሪም የሪፈራል ከፍተኛ የላቦራቶሪ ምርመራ አገለግሎት መስጠትና የእብድ ውሻ በሽታ የክትባት ምርት የማምረት ሃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በ2000.ዓ.ም አዲሱን የሥራ ሂደት ቀረጻ አካሂዶ ቀደም ሲል ተሰጥተውት የነበሩትን ተግባራትና ሃላፊነቶች እንዳሉ በተጨማሪ ሌሎች ኃላፊነቶችን በመጨመር በሦስት ዋና ዋና የስራ ሂደቶች እንዲደራጅ ተደረገ፡፡ አዲሱን የሥራ ሂደት እስከ 2006 ዓ.ም መተግበር ጀምረ፡፡ ነገር ግን በሥራ ሂደት የታዩ የህግ ከፍተቶችን ለማሟላትና ኢንስቲትዩቱ ከዓለም ዓቀፍ ግንኙነት አንጻርም ሊኖረው የሚገባውን የግንኙነት ደረጃ  ለማሳደግ ማቋቋሚያ ደንቡን እንደገና ማየት በማስፈለጉ በ2006 ዓ.ም “የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት” ተብሎ እንደገና ተቋቋመ፡፡ በአዲሱ ማቋቋሚያ ደንብም ሦስት ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶች ተሰጡት፡፡ እነርሱም፡

በአገር አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ምርምር አጀንዳ ላይ ተመስረቶ ቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸው የጤናና ሥነ-ምግብ ችግሮች ላይ ምርምር ማድረግና ሣይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ እውቀትን በማመንጨት፣ በመቅሰምና በማሰራጨት የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻል፣

2. የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥርን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ቅኝት በማካሄድ ስጋቶችን ቀድሞ መለየትና በቂ ዝግጅት በማድረግ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በተገቢ ሁኔታ መከላከል፣ ሲከሰትም ማንቂያ፣ ማስጠንቀቂያና ወቅታዊ መረጃ ማስተላለፍ፣ ፈጣንና ብቁ ምላሽ መስጠት እንዲሁም የተጎዳውን የህብረተሰብ ክፍል ከጤና አደጋው ተጽእኖ በፍጥነት እንዲያገግም ማድረግ፣

የኢንስቲትዩቱን ላቦራቶሪዎችን በሰለጠነ የሰው ሀይልና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ በማጠናከር ችግር ፈቺ ምርምሮችን ማካሄድ፣ለህብረተሰብ ጤና አደጋ ውጤታማ ምላሽ መስጠት፣ ሪፈራል ዲያግኖስቲክና አናሊቲካል ምርመራዎችን ማካሄድ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የጤናና የምግብ ሣይንስ ላቦራቶሪዎችን አቅም በመገንባት ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል የሚሉ ናቸው፡፡

The site where the Ethiopian Institute of Public Health is now located began to provide various public and animal health services in 1922 (1914 according to the Ethiopian calendar) from the time Dr. Thomas Lambie established an American volunteer medical service hospital. Dr. Thomas Lambe started the service with four doctors and six nurses who came with him. At that time, Dr. Thomas Lambe started educating women by opening a school called the American Mission, where only the women of our country could study. This service continued until the Italian invasion in 1928, according to the Ethiopian calendar.

When the Italian government invaded our country, the foreigners who were working in Ethiopia at the time were forced to leave the country by giving them compensation, so Dr. Thomas and his colleagues went to their home country, America. The services that were provided at the site were also stopped. Instead, the site was used by the Italian administration for Addis Ababa sanitary control services.

The Italian government tried to improve the services provided at Lambe Hospital by adding the Ethiopians who were working at the hospital at the time and its own experts. He then moved it to the area where the highway authority’s office is now located.

When Italy was defeated and left our country, institutions that had been providing various services by foreign experts before the Italian invasion were transferred to the property of the palace. As a result, the former Lambe Hospital was renamed Teferi Mekonon Hospital and was used as a treatment facility for the royal family.

In 1943, when the Ministry of Health of Ethiopia was established by decree, the medical services that were provided in the field were left and managed under the Ministry of Health. In 1944, the Ministry of Health entered into an agreement with the French government to conduct research and study on various diseases and to provide health laboratory testing services under the name “Institute Pasteur d’Ethiopi”. He was named and started his work by establishing various departments. This time the work was led by experts from both governments. The departments established to carry out research are:

  1. Department of Bacteriology, Parasitology and Serology,
  2. Department of Chemical Analysis,
  3. Department of Antipatriotic Vaccine Preparation,
  4. Director of Typhoid Vaccine Preparation,
  5. TB Vaccine Development Department,
  6. Rabies Vaccine Preparation Department, and
  7. Microvial Vaccine Development Department.

Among the vaccines that were produced in different quantities at that time:

  1. Antiviral vaccine
  2. Anti-typhoid,
  3. Rabies vaccine,
  4. TB vaccine,
  5. Typhoid vaccine,
  6. Yellow fever vaccine
  7. Flu vaccine included.

A certain amount was produced every year, and the service was given to the community for free.

This research and study, which started with the agreement of the French and Ethiopian governments, as well as the production and distribution of various vaccines, lasted until 1957.

The site, now home to the Ethiopian Public Health Institute, was known as the Dr. Thomas Lambe Hospital from 1915 to 1928 and was renamed the Pasteur Institute from 1944 to 1957. It is known by many people for its contributions to public health in Ethiopia.

After 1957, when the agreement between the government of Ethiopia and the government of France ended, the entire management and staff were to be managed by Ethiopians, and the budget was fully covered by the government of Ethiopia. The service that was provided earlier continued under the same name until 1977. However, except for the rabies vaccine, other vaccination services did not continue after the arrival of the Derg government.

 

After 1957, the research and study on the health problems of society, especially those that are contagious and occur suddenly, intensified. For example, in 1973, the institute conducted research that identified the cause of ergotism in the former Wolo province.

 

Since 1977, as the institute’s work has expanded, it was re-established as the Ethiopian National Health Research Institute. Dr. Fisseha Haile Meskel, who served as director from 1970 to 1985, contributed significantly to the institute’s overall development and the improvement and development of its relations with international institutions. The institute also opened a laboratory technology school during this time and produced many professionals in the field

It was initially established in 1962 as the Children’s Nutrition Department through cooperation between the Ethiopian government and the Swedish government. This department was later restructured in 1968 as the Ethiopian Institute of Nutrition. The institute was initially housed in the former Lelet Tananyework Hospital, now the premises of the Armed Forces Hospital. From 1968 to 1973, the institute undertook various activities to address the drought in Ethiopia. It also spearheaded the introduction of supplements known as Dobena Growth. Since 1973, the institute has operated from its own building, serving as the main laboratory and research institute, focusing primarily on food science and nutrition research. Dr. Zewdie Wolde Gabriel, who served as director for an extended period, played a key role in the institute’s development.

The Department of Traditional Medicine was established in 1979 by the Ministry of Health. To further strengthen its functions, the department was upgraded to the Department of Traditional Medicine Research. Since its establishment, the department has conducted research on medicinal herbs, compiling the national and scientific names of over 600 plants in Ethiopia and publishing them in a modern format. It has also conducted numerous studies and research on various traditional medicines.

With the establishment of the Ethiopian Health and Nutrition Research Institute and the Ethiopian Food Research Organization, it was recognized that consolidating similar and related activities in the health sector would enhance resource utilization and knowledge transfer.

The organizations were:

  1. Ethiopian National Health Research Institute
  2. Ethiopian Food Research Organization
  3. Traditional Medicine Research Department

The re-established Ethiopian Institute of Health and Nutrition’s mission was to conduct problem-solving research on priority public health issues and provide reliable health information to policy decision-makers. It was also tasked with providing high-quality referral laboratory testing services and manufacturing rabies vaccine products. In the year 2000, the institute revamped its work processes and added new responsibilities, organizing them into three main work processes.

These new work processes were implemented until 2006. However, to address legal gaps and enhance international relations, the institute was re-established in 2006 as the “Ethiopian Public Health Institute.” The new establishment regulation outlined three main duties and responsibilities:

Conducting research on health and nutritional problems based on the national public health research agenda, generating, absorbing, and disseminating scientific and technological knowledge to improve public health.

Collaborating with relevant parties to conduct surveys, identify health risks in advance, and make adequate preparations to prevent potential risks. When health risks occur, the institute is responsible for issuing alerts, warnings, and current information, providing a prompt and competent response, and assisting the affected society in recovering quickly from the impact.

Strengthening the institute’s laboratories with trained human resources and advanced technology to conduct problem-solving research, effectively respond to public health risks, perform referral diagnostic and analytical tests, build the capacity of health and food science laboratories at the national level, and ensure the provision of quality services.